|
ለ7ኛ ጊዜ የግብርና ምርት ዕድገትን ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ |
|
There are no translations available.
ለ7ኛ ጊዜ የግብርና ምርት ዕድገትን ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ለ7ኛ ጊዜ የግብርና ምርት ጭማሪ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ቢሮው ይህንን ያስታወቀው ለክልሉ ም/ቤት በ14ኛ መደበኛ ጉባዔ የ2ዐዐ2 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡
|
|
Read more...
|
|
|
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ የእቅድ አፈፃፀም አጥጋቢ እንደሆነና መሻሻል የተመዘገበበት እንደሆነ ተለገፀ፡፡ |
|
There are no translations available.
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ የእቅድ አፈፃፀም አጥጋቢ እንደሆነና መሻሻል የተመዘገበበት እንደሆነ ተለገፀ፡፡
የክልሉ መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ በ2ዐዐ1 በጀት ዓመትና በ2ዐዐ2 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት አቶ ለገሰ የኤጀንሲው ቦርድ ሰብሳቢ ለምክር ቤቱ አቀረቡ፡፡ የቦርድ ሰብሳቢው በዚህ ሪፖርታቸው በሚዲያዎች መደበኛ ሥራ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን፣ የየዘመኑ የትምህርት አከፋፈት ስነ-ስርዓት፣ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ በየደረጃው የተደረገው የተቀናጀ ጥረት፣ የጤና ኤክስቴንሽንና ሌሎች ከጤና ጋር የተያያዙ ስራዎች፣ በከተሞች ያለው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ የቀናጀ የቤቶች ልማት ኘሮግራም አፈፃፀምና ውጤት፣ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ስራዎች፣ ከልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ በየደረጃው የተጀመሩት የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስራዎች ሰፊ ሽፋን ተሰጥቷቸው መዘገባቸውን ገልፀዋል፡፡
|
|
Read more...
|
|
|
የቋሚ ኮሚቴው የሥራ ጉብኝት በሊቦከምከም |
|
There are no translations available.
የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት ከሚያረጋግጥበት አንዱና ዋነኛው ዘዴ አስፈጻሚውና የዳኝነት አካሉ የሚያከናወናቸውን ተግባራት አፈጻጻም በመገምገምና ለቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ነው፡፡ ይህ ተግባር በዋነኛነት ምክር ቤቱ ባቋቋማቸው አምስት ቋሚ ኮሚቴዎች ይከናወናል፡፡ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች እንደቀደሙት ጊዜያት ሁሉ የሥራ መነሻ እቅድና በመስክ የሚታዩ ተግባራት ላይ የትኩረት ነጥቦችን በመለየት ከጥር 23/2002ዓ.ም. ጀምሮ ለ13 ቀናት ወደተለያዩ ወረዳዎች ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በእነዚህ ቀናት የአንድ ከተማና የሶስት ገጠር ወረዳዎች የ2002 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በክልሉ እየተከናወኑ ካሉት ሰፋፊ የልማት ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የጣና በለስ ፕሮጀክት ተጎብኝቷል፡፡
|
|
Read more...
|
|
|